Author Archives: ethiotran@gmail.com

 • 0

እንኳን ደህና መጣችሁ

በቅድሚያ ወደ ድረ ገጻችን እንኳን ደህና መጣችሁ። ይህ ድረ ገፅ የተሰራው ከብዙ አመታት ልምድና  በደንበኞችን አስተያዬት ላይ በመመርኮዝ  ነው። ውክልና ቀልድ አይደለም ። በቅድሚያ አንድን ሰው ለወከል ከመሞከርዎ በፊት  ምን አይነት የውክልና ስልጣን ለተወካዩ እንደሚሰጡት በጥሞና ያስቡበት። ምክንያቱም በጣም አስቸጋሪው  የውክልና ስልጣን መስጠት ሳይሆን የውክልና ስልጣኑን ከተወካዩ ላይ ማውረዱ ወይም ማንሳቱ  ነው። ታዲያ እኛ ለደንበኞቻችን  የውክልና ስልጣን  መስጫም ሆነ መሻሪያ ሰነድ ለማዘጋጀት ያካበትነው ልምድ  ተጠቅሞ እርስዎን ከብዙ ውጣ ውረድ የሚያድን በጣም የተዋጣለት  ውክልና  ማዘጋጀቱ ፍቱን መድሀኒት ነው።
ስራችን  በአለም አቀፍ  ይዘት ሲኖረው የጄኔቫ እና የሄግ ህጎችን ተመርኩዞ የሚሰራ ስለሆን  ውክልናም ሆነ ሌሎች ሰነዶች ስናዘጋጅ  በማንኛውም አገር ባሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ ፍርድ ቤቶች፣ የኢሚግሬሽን ቢሮወች ፣ አየር መንገዶች፣ ኢምባሲወች፣ ባንኮች፣ ትምህርት ቤቶች እና የትምህርት ተቋማት፣ ዩንቨርስቲወች፣  ቀበሌወች፣ ክፍለ ከተሞች፣ ክልሎች፣ አስተዳደሮች፣ የጡረታ መምሪያዎች፣ የሴቶች ጉዳይ መምሪያ እና መሰል ቢሮወች፣  በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በመሬት አስተዳደር እና በመሳስሉት ቁልፍ ቦታዎች እንዲሰሩ ሆነው የረቀቁ ሰነዶች ናቸው ::

አላማችን  እርስዎ  ጉዳዮትን  በወቅቱ  እንዲያጠናቅቁ ነው:: ታዲያ ይህንን አገልግሎት በካሊፎርያ  ግዛት ብቻ ሳይሆን  በአራቱም የአለም ማእዘናት ተበትነው ለሚገኙ ወገኖች የአገልግሎቱ ተጥቃሚ  እንዲሆኑ ለማድረግ ይህንን እድል  ስንከፍት  በጣም  ደስተኞች  ነን ።

ለጥራት  ሲባል አሰራራችን  ወይም  ጠቅላላ  ሂደቱ ትንሽ  እረዘም  ያለ  ነው። ለዚህም በቂ ምክንያት አለን ::  ምክንያታችንም “ ሲሮጡ  የታጠቁት  ሲሮጡ  ይፈታል”  እንዳይሆን  ነው::  ታዲያ  የኛን  ስራ  በመጠቀም  ደንበኞቻችን  ከፈፀሟቸው ጉዳዮች መካከል ለምሳሌ ደንበኞቻችን፦

 • ልጆቻቸውን ወደ አሜሪካ አስመጥተዋል
 • የውርስ መብት አስክብረዋል
 • ቤትና ንብረት ሽጠዋል / ገዝተዋል
 • የንግድ ድርጅት ሽጠዋል / ገዝተዋል
 • ሆስፒታል፣ክሊኒክሰርተዋል
 • ቤት የንግድ ድርጅት፣ መኪና ማሽን አከራይተዋል
 • የጉዲ ፈቻ ውል ፈፅመዋል
 • የጋብቻ፣የፍቺ እና የልደት የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል
 • ኮንዶ፣ መሬት፣መኪና ተረክበዋል
 • ከባንክ ገንዘብም ማስወጣትም ሆነ ማስገባት ችለዋል
 • ከትምህርት ተቋማት የትምህርት ማስረጃ፣ዲፕሎማም ሆነ ዲግሪ አውጥተዋል
 • ብድር ተበደረዋል እንዲሁም ከፍለዋል
 • አክስዮን ገበተዋል የአክስዮን ድርሻ ተቀብለዋል
 • መብራት፣ውሃ ፣ የስልክ መስመር አስገብተዋል
 • ግብር ከፍለዋል

ከዚህ በላይ ያሉት ለአብነት ያክል የሚጠቀሱ ሲሆኑ  እኛ እርስዎ በፈለጉት መንገድ ያሰቡትን ጉዳይ የሚያሳካ  የውክልና ስልጣን እናዘጋጃለን። ዋናውና ትልቁ ሂደት ደግሞ የሚዘጋጀው የውክልና ስልጣን ይዘት ብቻ ሳይሆን ያ ውክልና  በኢትዮጵያም ሆነ በማንኛውም የአለም ክፍል  ተቀባይነት እንዲኖረው የሚደረገው   ሂደት ነው። ይህ ሂደት እርስዎ እንዳለወት የዜግነት እና የመኖሪያ ፈቃድ ሁኔታ  ሂደቱ የሚወስደው ጊዜ ሊያጥርም ሆነ ሊረዝም ይችላል ። ይህ ማለት ለምሳሌ  የአሜሪካ ዜግነት ያለው ኢትዮጵያዊና  ሰውና ቀኑ ያልተቃጠለ  የኢትዮጵያ ፓስፖርት ያለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ውክልናውን ለማጠናቀቅ የሚወስደው ጊዜ በጣም ይለያያል።

ታዲያ  የኛ ዋናው ስራ የውክልና ስልጣኑ ከተዘጋጀ  በኃላ ውክልናው ህጋዊ እንዲሆን የሚያስፈልጉ ነገሮችን  ማሟላት ነው።  የሰነዱን ህጋዊ ለማድረግ ሂደት ማሟላት ጋር በተየያዘ ቅደም  ተከተል  ድርጅታችን  ምን ምን ማድረግ እንዳለብዎ ሁሉንም  ነገር እናስፈፅማለን። ከነዚህም አገርልግሎቶ ውስጥ በጥቂቱ

ኖተሪ ፓፕሊክ

ኣፖስታይል

ኣቶኔሽን

በስቴት ዲፓርትመን ማህተም ማስመታት

በሴክራተሪ ስቴት ማህተም ማስመታት

በቲትዮጵያ ኢምባሲ ማህተም ማስመታት

የኢትዮጵያ ፓስፖርት የማውጣት ሂደት መርዳት

የትውልድ ኢትዮጵያዊ ሂደት መርዳት

የትርጉም አገልግሎት መስጠት ይገኙበታል

በበለጠ ለመረዳት እባክ ዎ በስልክ ቁጥር  619 255 5530 ይደውሉልልን::

እናመሰግናለን።


 • 1

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ይህን ያውቁ ኖሯል? በውክልና ከዚህ በታች የእርስዎ  ተወካይ  እርስዎን በመወከል ማከናወን እንደሚችል

 • በስምዎ ተመዝግቦ የሚገኘውን የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ተወካይ እንደ  እንዲጠብቁ፣እንዲቆጣጠሩ፣ እንዲያስተዳድሩ፣ እንዲሸጡ፣ እንዲለውጡ፣ እንዲያከራዩ፣ እንዲያኮናትሩ፣ ውል እንዲዋዋሉ፣ገንዘብና ሰነድ ፈርመው እንዲቀበሉ፣
 •   አዲስ የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ፣ የተከፈተውንም የባንክ ሂሳብ እንዲያንቀሳቅሱ፣ ገንዘብ እንዲያስገቡ፣እንዲያወጡ፣ ቼክ ፈርመው መስጠትም ሆነ መቀበል እንዲችሉ፣
 • ጨረታ እንዲጫረቱ፣ የጨረታ ውል እንዲዋዋሉ፣
 • የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት እነዲገዙ፣ ስሙን እንዲያዛውሩ፣ ሊብሬ እንዲያዎጡ፣ ቦሎ ከላውዶ እንዲያስደርጉ፣
 •   በማህበር ተደራጅተውም ሆነ በሊዝ ቦታ ተመርተው ቤት እንዲሰሩ፣ የግንባታ ፍቃድ እንዲያዎጡ፣ ግንባታዎችን እንዲያካሂዱ፣ ለግንባታ የሚያስፈልጉ ማቴሪያል እንዲረከቡ፣ ስብሰባዎች እንዲሰበሰቡ፣ ድምፅ እንዲሰጡ፣ የአባልነት መታዎቂያ እንዲያዎጡ፣  የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ካርታ ፕላን፣ የፕላን ማሻሻያ እንዲያወጡ፣
 • መብራት፣ ውሃ ስልክ እንዲያስገቡ፣ የሚከፈሉ ክፍያዎችን እንዲከፍሉ፣
 • ከውጭ የሚጣውን ማንኛውንም አይነት እቃም ሆነ መኪና በሚመለከተው የግምሩክ መ/ቤት በመቅረብ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ በማሟላት መረከብ እንዲችሉ፣
 • ሰሌዳ እንዲያስቀይሩ፣ ሊብሬ እንዲያወጡ፣
 • የንግድ ፈቃድም ሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንዲያዎጡ፣ እንዲያድሱ፣ አስፈላጊም ሆኖ ሲገኝ ተመላሽ እንዲያደርጉ፣ የንግድ ዘርፉን እንዲለውጡ፣
 • አክስዮን እንዲገቡ፣ ኩባንያ እንዲያቋቁሙ፣ በመመስረቻ እና በመተዳደሪያ ጉባኤ ላይ እንዲፈርሙ፣ ስብሰባዎችን እንዲሰበሰቡ፣ ድምፅ እንዲሰጡ፣ የአክስዮን ድርሻዎትን እንዲሸጡ፣ እንዲለውጡ፣ እንዲገዙ፣
 • ከማንኛውም የትምህርት ተቋም በመቅረብ ማንኛውንም የትምህርት ማስረጃዎትን እንዲቀበሉ፣ የትምህርት ማስረጃዎትን ከሚመለከተው ክፍል እንዲያዎጡ፣ ሰነድ ላይ ፈርመው መስጠትም ሆነ መቀበል እንዲችሉ፣
 • የልደት ወረቀት እንዲያወጡ
 • የጉዲ ፍቻ ውልን በተመለከተ እርስዎን ወክለው እንዲያስ
 • በእጣም ሆነ በምዝገባ ማንኛውንም ጉዳይ እንዲመዘገቡ፣
 • የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረትዎን በዋስትና አስይዘው ከባንክም ሆነ ከአበዳሪ ድርጅቶች ገንዘብ እንዲበደሩ፣ የብድር ውል እንዲዋዋሉ፣
 • በስምዎም ሆነ በንብረትወ ላይ ክስ ክርክር ቢነሳ ቢችሉ እራሳቸው ከአቅም በላይ ከሆነ ደግሞ የህግ ጠበቃ ይዘው ለመከራከር፣ አቤቱታ ለማቅረብ፣ መልስ ለመስጠት፣ ይግባኝ ለማለት እንዲችሉ፣ ቃለ መሃላ ፣ አቤቱታ እንዲያቀርቡ፣ የውሳኔ ሰነዶችን እንዲቀበሉ፣ አፈፃፀም እንዲቀበሉ፣ አስፈላጊም ሆኖ ሲገኝ ሌላ 3ኛ ወገን እንዲወክሉ፣ እንዲሽሩ፣
 • በአጠቃላይ በመንግስታዊ መ/ቤትም ሆነ በህዝባዊ ድርጅቶች እንዲሁም በአስተዳደር መ/ቤት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኢምባሲዎች፣ በግምሩክ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በመብራት ሃይል፣ በስራና ከተማ ልማት ቢሮ፣ በቀበሌ፣ በክፍለ ከተማ፣ በኢትዮ ሞባይል መምሪያ፣ በውሃና ፍሳሽ አገልግሎት፣ በመሬት አስተዳደር በመቅረብ ጉዳዮትዎን በመከታተል እንዲፈፅሙና መወከል እንደሚችሉ